ከመቅደላ ተዘርፎ የሄደው አስገራሚው የኢትዮጵያ ቅርስ ያለበት ቦታ ታወቀ፡፡ ሰለ ቅርሱ ከበሬታና ታሪካዊነት የተደረጉ ውይይቶችን ይመለከቱ፡፡
በምርምር ሥራቸው ተሸላሚ የሥነ ዐዕምሮና የነርቭ ስፔሻሊስት ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ ከዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ ጋር የተደረገ ውይይት፡፡ በዕድሜ ከመርሳት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ለመከላከል ማድረግ የሚገባዎት ነገሮችን የሚጠቁም ጥናት ውጤት፡፡ እርጅናን የሚያስቡ ከሆነ ውይይቱን ይመልከቱ ወይም አዳምጡ፡
ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ ከሚከተሉት የጤና ቀውሶች አንዱ የኩላሊት በሽታ ነው፡፡ ይህንን የኩላሊት በሽታ ከፋ ደረጃ እንዳይሻገር የሚደረጉ ነገሮች አሉ፡፡ በአብዛኛው፣ አስካሁን ድረስ የሚደረገው፣ ለኩላሊት በሽታ ጠንቅ የሆኑትን የደም ግፊትና የሰኳር በሽታን በመድሀኒት አማካኝነት መቆጣጠር ነው፡፡ ይህ ግን በራሱ፣ እነዚህ በዕደሜ የገፉ ሰዎችን ከሚገባው በላይ ብዛት ያላቸው መድሐኒቶች እንዲወስዱ፣ አንዳንዴም በመድሐኒቶች ምክንያት ጉዳቶች አንዲከሰቱ ነው ያደረገው፡፡ ጥያቄው ታዲያ፣ መድሐኒት ከመስጠት ውጭ ሌላ ምን አይነት ፕሮገራም፣ የኩላሊት በሸታን ወደከፋ ደረጃ ከመድረስ የሚቀነስ ነገር አለ ወይ ነው፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
ዕድሜያቸው ከ45 አመትና ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች ሊያነቡት የሚገባ አዲስ የአንጀት ካንሰር ቅድሚያ ምርመራ (screening) መመሪያ
ለዚህ አዲስ የአንጀት ካንስር ቀድሚያ ምርመራ መለወጥ ምክንያት በ43 አመቱ ሕይወቱ ያለፈው የሲኒማ ተዋናይ ነው፡፡ ብላክ ፓንተር የሚባለውን ሲኒማ ያየ ሰው ኮከብ ተዋናዩን ያስታውሳል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
መሀል ደረትዎ ውስጥ የሚያቃጥል ህመም የሚሰማዎት ከሆነ ይህን ማንበብ ሊረዳዎት ይችላል ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
ጎሽ የጤና ትምህርትና ምክር በአማርኛ
አዘጋጅና አቅራቢ ዶ/ር ገበየሁ ተፈሪ
የአጼ ምኒልክ እውነተኛ ድምፅ
ትምህርት ልናገኝበት የሚገባው በራሳቸው በአጼ ምኒልክና
በህዝቡ የተከበረው የአድዋ 7ኛ አመት መታሰቢያ ታሪክ ባጭሩ
ሁሉም ሰው ሊያውቀው የሚገባ በሰው ዘር ላይ ወንጀል መፈፀም
የተባበሩት መንግሥታት መመዘኛ
Amazing documentaries about Ethiopia - Must Watch
የመጽሐፍ ትረካ 1 መቅደላ የቴዎድሮስ ዕጣ
ስለ አጼ ቴዎድሮስ ያልተሰሙ ያልተነገሩ ዕውነታዎች
ሰለ መቅደላ ዘመቻና ሰለ ንጉሡ ፍፃሜ በዝርዝር
ይህንን መጽሐፍ ከላነበቡ ወይም ካላዳመጡ ስለ አጼ ቴዎድሮስ በቂ ዕውቀት…
ስለ መጽሐፉ የተሠጡ አስተያየቶችን ለማንበብ
ክፍሎችን ለማዳመጥ ከታች ያሉትን ይጫኑ
Copyright 2013. Gosh Health.
All Rights Reserved.
የፈለጋችሁትን በሉ እንጅ ባናለቅስም የተሰማን ጭንቀት ይህ ነው አይባልም፡፡ አዎ ሀኪሞች አንጨነቃለን ግን እንድታውቁብን አንፈልግም፡፡
የሞርጋን ፍሪማን “Finding God” የሚባል ፕሮግራም በናሽናል ጂኦግራፊክ ፕሮግራም እያየሁ እያለ፤ በጨረፍታ ከ9/11 ተረፍኩ የሚል ሰው አየሁኝ፡፡ በአውሮፕላኑ ከጋዩት ህንፃዎች አንደኛው ላይ የነበረ ሰው ነው፡፡ መደምደሚያው እግዚአብሔር አለ ነው፡፡ ድንገት ጋምቤላ ያጋጠመኝ አንድ ሁኔታ ብልጭ አለብኝ፡፡ ልፃፋው አልፃው እያልኩ አመናታሁና ግን ይኸው፡፡
ከህክምና እንደተመረቅሁ ጋምቤላ ተመድቤ ስሰራ በድንገት የስራ ጓደኞቼ በሰበብ አስባቡ ወደ አዲስ አበባ ሄዱና 100 አልጋ ላለው ሆስፒታል ብቸኛ ሀኪም ሆንኩኝ፡፡ ይህ ሁኔታ መቱ(ኤሊባቡር) ባሉ አለቆች ስለታወቀ ከጎሬ አንድ ሀኪም ለርደታ ተላከልኝ፡፡ አብሬው የተማርኩ በጣም የምወደውና የማከብረው ልጅ ነበር፡፡ (ፈጣሪ በሰማይ ነብሱን ይማረው) ደስታዬ መጠን አልነበረውም፡፡ እንግዲህ ጋምቤላ ሆስፒታል ለኗሪው ብቻ ሳይሆን በሰፈራ መንግሥት ጋምቤላ ላመጣቸው ከሰማንያ ሺ በላይ የሚሆኑ ሰፋሪዎችና ግፋ ሲል ደግሞ ከሁለት መቶ ሺ በላይ ለሚሆኑ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች አገልግሎት መሰጠት አለበት፡፡ ስደተኞቹ እንኳን ኢታንግ የሚባል ቦታ የራሳቸው አልጋ ያለበት ጤና ጣቢያ ይረዳሉ፡፡
ለሠፋሪዎቹ ግን ሀላፊነቱ የኛ ነበር፡፡ በደርግ ጊዜ ነበር፡፡ አንድ የማይረባ ህግ ነበር፡፡ በጣም አሰቃቂ ውጤት ነው ያስከተለው፡፡ በምንም መንገድ ቢሆን ሠፋሪዎች ቢታመሙና ከፍተኛ ህክምና ርደታ ቢያስፈልጋቸው ከጋምቤላ ውጭ መላክ አይቻልም፡፡ በጭራሽ፡፡ ቀጭን ትዕዛዝ ነበር፡፡
ታዲያ ከጎሬ የመጣው ጓደኛዬ ጋር ሆነን የምንችለውን ያህል ሠርተን ልንወጣ ስንል ድንገት ወሊድ ክፍል ምጥ ላይ ነች የተባለች ሴትዮ አለች ተብሎ ተጠራን፡፡ ደም እየፈሰሳት ነው፡፡ ምጥ ላይ አልገባችም ግን ቀኑ ደርሶአል፡፡ ምርመራ ስናደርግ ማንም ሀኪም ሊያጋጥመው የማይፈልግ ሁኔታ ነው ያየነው፡፡ እንደቆምን ደነዘዝን፡፡ ነገሩ የእንግዲህ ልጅ ተብሎ የሚጠራው በህክምና ፕላሴንታ የሚባለው ነገር ከልጁ ፊት ለፊት የማህፀን መውጫው ላይ ተቀምጧል፡፡ ይህ በጣም አደገኛ ሁኔታ ነው፡፡ ምክንያቱም በተፈጥሮ መጀመሪያ ልጁ ይወለድና ከዚያ የእንግዲህ ልጁ ተከትሎ ነበር መምጣት ያለበት፡፡ አለበለዚያ ገና ልጁ ሳይወለድ የእንግዲህ ልጁ ከማህፀኑ ግድግዳ ከተላቀቀ እናትና ልጁ በደም መፍሰስ ምክንያት ህይወታቸው ያልፋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ደግሞ መነካካት ያባብሰዋል፡፡ የነበረው አማራጭ በኦፕራሲዮን ማሰወለድ ነው፡፡ እኔና ጓደኛዬ መሥራት እንችል ይሆናል፡፡ ስንማር ይህን ሁሉ ተምረናል፡፡ ባይሆን አስተማሪ በሌለበት ብቻችን አድርገነው አናውቅም፡፡ ለዚያም ቢሆን ማደንዘዣ የሚሠጥ ባለሙያ የለም፡፡ ነገሩን ሲያከፋው ደግሞ ሴትዮዋ ደም ማነስ አለባት፡፡ የደም ማነሱ መጠን ደግሞ ከጤናማው መጠን ከግማሽ በታች ነው፡፡ ወደ መቱ እንዳንልክ አምቡላንስም የለም፡፡ የደርግ ቀጭን ትዕዛዝ ደግሞ ከላይ እንደተጠቀሰው ነው፡፡ የፈለጋችሁትን በሉ እንጅ ባናለቅስም የተሰማን ጭንቀት ይህ ነው አይባልም፡፡ አዎ ሀኪሞች አንጨነቃለን ግን እንድታውቁብን አንፈልግም፡፡
ከሴትዮዋ አልጋ ስር የተደገነው ሰሀን ላይ የሚንጠባጠበው ደም ድምፅ እሰካሁን ድረስ ይህ ሁኔታ ትዝ ባለኝ ቁጥር ጠብ ጠብ ጠብ ሲል ይሰማኛል፡፡
እኔና ጓደኛዬ ተያየን፡፡ ንግግር አላስፈለገንም በሚገባ አውቀናል፡፡ ሴትዮዋ ከነልጇ መሞታቸው ነው፡፡ ድንገት ደም ቢያስፈልግ ደም የሚሠጥ ሰው ጠፋ፡፡ ባል ተብየው ሲጠየቅ ሚሰት ቢሞት ሌላ ይተካል እንጅ ደም አልሠጥም አለ፡፡ በባህላቸው ደም መሥጠት አይወዱም፡፡ ጭራሽ ተሠወረ፡፡
ምን እናድርግ?
ቆየን፡፡ ተጠማዘዝን፡፡ መጨረሻ ወደ መኖሪያ ቤታችን ሄድንና፤ ሆስፒታሉ አጠገብ ነበርን፡፡ አንደ አዲስ ነገር ቢፈጠር ጥሩን አልን፡፡
ግን ቤት እንደገባን ሳንነጋገር ሁለታችንም እኔ አልጋ ሥር ተንበረከክንና ወደ እግዚአብሒር ፀለይን፡፡ ለሴትዮዋ፡፡
ምንም ጥሪ ስላልመጣና ሰለደከመን የሚቀመሰውን የወንደላጤ ምግብ በልተን ጋደም እንዳልን እንቅልፍ ለቀቀብን፡፡ ሌሊቱኑ በሙሉ ምንም ጥሪ አልመጣም፡፡
በጥዋት ሁለታችንም እየሮጥን ወደሴትዮዋ ሄድን፡፡ ነርሷ በፈገግታ ተቀበለችን፡፡ ተመስገን፡፡ ሌሊቱን ሴትዮዋ የእንግዲህ ልጁንና ልጁን አንድ ላይ ገፍታ ወልዳ ከሞት ተርፈዋል፡፡ ማህፀን የእንግዲህ ልጁ እንደወጣ ወዲያውኑ ሰለሚኮማተር ደም መፍሰስ ይቆማል፡፡ ግፋ ቢል ማህፀኑ እንዲኮማተር የሚያደርግ መድሀኒት መሥጠት ነው፡፡ ግን ሁለቱም ማለትም ልጁም የአንግዲህ ልጁም መውጣት አለባቸው፡፡
እንግዲህ ተዐምር ማለት ይህ ነው፡፡ ሴትዮዋ ከነ ልጇ ከነደም ማነሷ በዚህ የህይወት መጥፊያ ሁኔታ ተረፈች፡፡
ተመስገን፡፡
የመጽሐፍ ትረካ 2
ኢትዮጵያ ባውሮፓ ዲፕሎማሲ እንዴት ተረፈች?
የአባይ ወንዝ ችግር መንስኤ
የአድዋ ጦርነት መንስኤ
ደረጃ (ትርጉም) | Hgb A1c % | FBS (mg/dl) | OGTT (mg/dl) |
ጤናማ | Below 5.7 | 99 or below | 139 or below |
ቅድመ ሰኳር በሽታ | 5.7 to 6.4 | 100 - 125 | 140 - 199 |
የስኳር በሽታ | 6.5 or above | 126 or above | 200 or above |
FBS= Fasting Blood Sugar
OGTT= Oral Glucose tolerance Test
ከኤች አይ ቪ (HIV) ፈውስ ማግኘት ቀላል ነገር አለመሆኑን ከተገነዘብን ሰንብተናል፡፡ ከዚሀ ቀደም ሁለት ሰዎች ብቻ ናቸው ከዚህ ቫይረሰ ተፈውሰው መድሐኒት መውሰድ ያቆሙት፡፡ የመጀመሪያው ሰው የበርሊን ሰውዬ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከኢንግላንድ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች የተፈወሱበትን መንገድ ወይም ዘዴ ተከትሎ ሙከራዎች ቢደረጉም አልተሳካም፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
ይህንን ርእስ ከዚህ በፊት መጠነኛ ገለፃ ለመስጠት ሞክሬ፣ ነገር ግን በየጊዜው ለውጦች ሰለመጡ ፋታ ልስጥ ብይ ሰጠብቅ፣ አንድ ወዳጄ ከአዲስ አበባ የፌስ ቡክ ርዕስ ላከልኝና ሰመለከት በጣም አዘንኩኝ፡፡ የፌስ ቡክ ለጣፊው፣ ትንሽ በደንብ ቢያነቡ እንዲሕ አይነት መረጃም ባለጠፉ ነበር፡፡ ይህ ፖለቲካ አይደለም፣ ሳይንስ ነው፡፡ በኮቪድ በሀሰት የምንታመሰው ይበቃል፡፡ እናም፣ ጉዳዩን ላስተካክል ብዬ ይህን ፅሁፍ አቅርቤያሁ፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
በወሬ በወሬ እየሰማን ጉዳዩን ብዙም ትኩረት አልሠጠነውም ነበር፡፡ የሚያመክን ክትባት አለ ሲባል፣ የመጀመሪያው ጥያቄ ውነት ነው ወይ የሚለው ነው፡፡ ከጓደኛዬ ጋራ ሀሳብ ስንለዋወጥ፣ ክትባቱ በስህተት ማምከን የሚችል መድሐኒት ጋር ተነካክቶ ይሆናል ወይም እንደዚያ የሚባል ነገር ሰምቻለሁ ነው፡፡ ነገሩ ትንሽ የሚከነክን ስለሆን በወሬ በወሬ ሳይሆን በሳይንሳዊ መንገድ የተሠሩ ጥናቶችን ለእንባቢ የሚያቀርቡ የህክምና ወይም የጤና መፅሔቶችን ማገላበጥ ጀመርኩ፡፡ እና እራሴንም አስከሚገርመኝ ድረስ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ፅሑፍ አገኘሁ፡፡ ለካስ አዳማጭና አንባቢ ጠፍቶ ነው እንጂ ለወሊድ መከላከያ የሚሆነው ክትባት ከተሠራ ስንብቷል፡፡
በአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1993 የታተመው አናልስ ኦፍ ኢንተርናል ሜዲሲን የሚባል መፅሔት ላይ በቁጥር Ann Med. 1993 Apr;25(2):207-12 ላይ የወጣ መረጃ በዚያን ጊዜ በህንድ አገር ለዚሁ ወሊድ ለመከላከል ታስቦ የተሠራ ክትባት እንዳለ ይገልፃል፡፡ ለተጨማሪ ንባብ ይህን ይጫኑ
Community health
education in Amharic
በቀን አራት ሺ ርምጃዎችን መራመድ የመሞት አጋጣሚን ይቀንሳሉ
አስተውላችሁ ከሆነ፣ በስልክ፣ በእጅ ሰአት ወይም ደግሞ ራሳቸውን የቻሉ ርምጃን የሚቆጥሩ መሳሪያዎችን የሚገለገሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ እርስዎም ተገልጋይ ይሆናሉ፡፡ ነገሩ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ እንደኔ አመለካካት ስንፈጠር፣ ተንቀሳቅስን ጤናማ መጠነኛ ምግብ ከተመገብን ክምግብና ካለመንቀሳቀስ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ለሞት ከሚዳርጉ በሽታዎች እየራቅን እንሄዳለን፡፡
አንግዲህ በመረጃ የተደገፉ ምክሮችን ማካፈል ተገቢ ስለሆነ፣ ርዕሱን በሚመለከት የቀረበ ጥናት ላካፍላችሁ፡፡
ዋናው ነገር በጠንካራ መረጃዎችም የሚታወቀው፣ የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግና በጣም ውሱን የሆኑ ርምጃዎችን መራመድ ለደም ሥርና የልብ ሕመም ከማጋለጡም በተጨማሪ ባጠቃላይ ለጤና መታወክ ሰበብ ነው፡፡
ነገር ግን፣ መራመድ ካለብን በቂ የሆኑ የርምጃዎች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ከዚህ በፊት አይታወቅም፡፡ ያም ይህ የማካፍላችሁ ጥናት እስከሚወጣ ድረስ ነው፡፡ European Journal of Preventive Cardiology በተባለ መፅሄት በታተመው ጥናት፣ አጥኝዎቹ ያደረጉት ነገር፣ በቁጥር ምን ያህል ርምጃዎች ከአጠቃላይ ሞት ምክንያቶች በተለይም ከደም ሥርና ልብ ህመም ጋር በተያያዙ ምክንየቶች የመሞት አጋጣሚ ጋር ግንኙነት መኖሩን ማወቅ ፈለጉ፡፡
ያደረጉትን ነገር በአማካይ ለሰባት አመታት ክትትል ያደረጉ የአስራ ሰባት ጥናቶች ውጤቶችን ባንድ ላይ መገምገም ነው፡፡ የጥናቶቹ ተሳታፊዎች ቁጥር 226889 ሲሆን፣ ሰዎች ጤናማ የሆኑና ለደም ሥርና ለልብ በሽታ የመጋለጥ አደጋ ወይም ጠንቅ ያለባቸው ነበሩ፡፡
ጥናቱ እስከ ጁን 2022 ድረስ ባለው ጌዜ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡ ወደ ውጤቱ ስንመለስ በየጊዜው በቀን የአንድ ሺ ርምጃዎችን መጨመር፣ በሁሉም አይነት ለሞት በሚዳርጉ ሁኔታዎች መሞትን በአስራ አምስት ከመቶ (15%) የቀነሰው መሆኑን ይገልጣሉ፡፡ በቀን ርምጃዎችን በአምስት መቶ መጨመር እራሱ በደም ሥርና በልብ ህመም ምክንያት መሞትን በሰባት ከመቶ (7%) ይቀንሳል፡፡ በቀን የርምጃዎች ቁጥር በምድብ ተከፋፍሎ ሲታይ፤ ምድብ አንድ በአማካይ በቀን 5537 ርምጃዎች፣ ምድብ ሁለት፣ በቀን በአማካይ 7370 ርምጃዎች፤ ምድብ ሶሰት ደግሞ በቀን በአማካይ 11 529 ርምጃዎች፣ በማንኛውም ጠንቅ የመሞት አደጋዎች የቀነሱ መሆናቸውን ያብራራሉ፡፡ በምድቦች ሲታይ፣ ምድብ አንድ በ48 በመቶ፣ ምድብ ሁለት በ55 በመቶ እናም ምድብ ሶሰት በ76 ከመቶ ነው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው በየቀኑ የሚራመዱት የርምጃ ቁጥር በጨመረ ቁጥር፣ ጠቀሚታው እየጨመረ ይሄዳል፡፡
በቀን አነስተኛ ርምጃ ተብሎ የተቆጠረው (1594 – 4000 ርምጃዎች) አማካይ 2337 ርምጃዎች እንደማነፃፀሪያ ተወስዶ ከሌሎች ምድቦች ጋር ሲወዳደር፣ በሌላ አመዳደብ ቁጥር አንድ አማካይ 3982 ርምጃዎች፣ ቁጥር ሁለት በቀን አማካይ 6661 ርምጃዎች፣ ቁጥር ሶስት ደግሞ በቀን በአማካይ 10413 ርምጃዎች በቀጥታ በደም ሥርና በልብ ህመም ሰበብ የመሞት አደጋውን፣ ቁጥር አንድ ምድብ በ16% ከመቶ፣ ቁጥር ሁለት ምድብ በ49% ከመቶ፣ ቁጥር ሶስት ምድብ ደግሞ በ77% ከመቶ ይቀንሳሉ፡፡
አጥኝዎቹ ሲያጠቃልሉ፣ በቀን ጠቃሚ የርምጃዎች ቁጥር ከመጠነኛው 3967 (አራት ሺ ሲጠጋጋ) በላይ፣ በደም ሥርና በልብ ህመም ሰበብ ይሁን በሌላ ሰበብ የመሞት አደጋው ይቀንሳል፡፡ ለደም ሥርና የልብ ህመም ሰበብ ደግሞ መጠነኛው መነሻ የርምጃዎች ቁጥር ጠቀሚታ የታየው ከ2337 በላይ ሲሆን ነው፡፡
ከአየር ሀይሎች መዝሙር ትንሽ ለወጥ ብናደርግ፣ ተነሳ ተራመድ ልብህን አበርታ … ርምጃ የሚቆጥሩ መሣሪያዎች በያይነቱ አሉ፣ በአማዞን ዋጋቸው መጠነኛ የሆኑ ርምጀዎን የሚቆጥሩ በኪስ ውስጥ የሚያዙ ወይም ባንገት የሚንጠለጠሉ ወይም ቀበቶ ወይም ሱሪ ላይ ሻጥ የሚደረጉ አሉ፡፡ እኔ የግሌን የምመከረው ከሌላ ዳታ ቤዝ ጋር ከተያያዙ አፖች ይልቅ እንዚህ ከምንም ሌላ ፕሮገ ፀራም ጋር ያልተያያዙትን መጠቀም ይበጃል፡፡ ለምንድነው የማላውቀው ሰው የኔን ርምጃና ሌላም መረጃ የሚሰበስበው? ለማንኛውም በየቀኑ የሚየሄዱትን የርምጃ ቁጥር ከሚችሉ ከመጠነኛ ቁጥር ተነስተው፣ መጨመር ሲፈልጉ ግን መዳረሻውን በአንድ ሺ ርምጀዎች መጨመር ከፍተኛ ጠቀሚታ አለው፡፡
በነገራችን ላይ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ለአካል ጤንነት ብቻ ሳይሆኑ ለአእምሮ ጤንነትም ይረዳሉ፡፡ በዕድሜ ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን የመዘንጋት ወይም የመርሳት ሁኔታን ያዘገያሉ፡፡ ይህ በጥናት የተደገፈ ውጤት ነው፡፡ ከፕሮፌሰር ዮናስ ገዳ ጋር የተደረገውን ውይይት በድረ ገፁ ይመልከቱ፡፡
መንቀሳቀስ ለጤንነት ይበጃል፣ እንኳን ለጤንነት ላገርም ይበጃል፡፡
መልካም ንባብ (አካፍሉ)